በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ክልል ከ16 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ስራ ላይ ናቸው
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ክልል ከ260 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸውን የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለፀ
የቢሮ ሃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ እንደተናገሩት መንግሰስት በኢንቨስትመንት ዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡
በክልሉ ኢንቨስትመንትን የማነቃቃት ስራዎች በስፋት በመከናወናቸው ቀደም ሲል ከነበሩ 655 ፕሮጀክቶች በተጨማሪ በለፉት 3 ዓመታት ብቻ 263 አዳዲስ ፕሮጀክቶች ከ16 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል አስመዝግቦ ወደ ስራ መግባታቸውን ገልፀዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ ለ1ሺህ 500 ቋሚና ከ90ሺህ ለሚበልጡ ዜጋዎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።
በዘረፉ ፈጥኖ ወደ ስራ የገቡትን ባለሃብቶችን የመበረታታትና የመደገፍ ስራ መሰራቱንም ጠቁመዋል፡፡
በአንጻሩ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ወደ ስራ ያልገቡ 12 ባለሃብቶች መኖራቸውን አቶ ተመስገን ገልጸው ለእንዚህ ባለሃብቶች የተላለፈ 18ሺህ ሄክታር መሬት በማስመለስ ወደ መረት ባንክ ማስገባት መቻሉንም ገልፀዋል
ዘጋቢ ፡ በየነ ወርቁ ከሚዛን ቅርንጫፍ
More Stories
ገቢ ከራስ ለራስ የሚዉል በመሆኑ በቴክኖሎጂ በተደገፈ የአከፋፈል ስርዓት በአጭር ቀናት ከታቀደው በላይ ግብር መሰብሰብ እንደሚገባ ተገለጸ
የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ግብርን በመክፈል የበኩላቸውን ኃላፊነት እየተወጡ መሆኑን አንዳንድ የገደብ ከተማ ነጋዴዎች ገለጹ
ባለፉት 11 ወራት ከ2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ