በየአካባቢው ስኬታማ የሆኑ ሀሉ አቀፍ የልማት ተግባራትን ወደ ህዝቡ በማስፋፋት የኢትዮጵያ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል ተጠቆመ

በየአካባቢው ስኬታማ የሆኑ ሀሉ አቀፍ የልማት ተግባራትን ወደ ህዝቡ በማስፋፋት የኢትዮጵያ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል ተጠቆመ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በየአካባቢው ስኬታማ የሆኑ ሀሉ አቀፍ የልማት  ተግባራትን ወደ ህዝቡ በማስፋፋት የኢትዮጵያ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል በኣሪ ዞን 3ኛ ዙር አመራር ስልጠና የተሳተፉ አካላት ገለፁ።

“የህልም ጉልበት፣ ለእምርታዊ ዕድገት” በሚል መሪ ቃል የተሳተፉ 3ኛ ዙር አመራሮች በዞኑ በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ መስክ ምልከታ አካሂደዋል።

በአመራሩ የተጎበኘው በአካባቢው አጠራጣር ኩሬ ቀበሌ ጥላ ማኑዩፋክቸርንግ አክሲዮን ማህበር የለማ የበቆሎ ምርጥ ዘር ማባዣ ጣቢያ ሲሆን ማህበሩ 15 ሄክታር ምርጥ ዘር መልካሳ 2 እና ፓዮነር የተሰኙ ዝርያዎችን እያባዛ እንደሚገኝ የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አውግቸው ዘውዴ አስረድተዋል።

4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር መነሻ ማህበሩ ከ80 ባልበለጡ አባላት ተቋቁሞ በአሁን ወቅት ከ2 መቶ በላይ አባላት ያሉትና ካፒታላቸውም ከ10 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱን ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።

የኣሪ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አስፋው ዶሬ በበኩላቸው፤ ከዚህ ቀደም ለመንግስትና ፓርቲ አመራሮች የተሰጠው ስልጠና  ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን በተጨባጭ መመልከት ተችሏል ብለዋል።

በመስክ ምልከታው ከበቆሎ ዘር ብዜት በተጨማሪ የኤሶል 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤትና የጂንካ ኮሪደር ልማት ተካቶ ጉብኝት ተደርጓል።

ሰልጠኝ አመራሮች በመስክ ምልከታ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልፀው በቁርጠኝነት መሥራት ከተቻለ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዲሚቻል በምልከታው ያዩት ምስክር መሆኑን ገልፀዋል።

ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱም መሰል ተግባራትን በተሻለ የማስፈፀም አቅም ህዝቡን አቀናጅተው እንደሚሠሩ አመላክተዋል።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን