የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የስራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት የንቅናቄ መድረክ ማካሄድ ጀመረ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ “ክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ ለዕመርታዊ ዕድገት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚያካሂደው የንቅናቄ መድረክ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት መካሔድ ጀምሯል።
በመድረኩ በኢንተርፕራይዞች የተሰሩ ስራዎችን የሚዳስስ ቪዲዮ ለዕይታ የሚቀርብ ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪ የስራ እድል ፈጠራ ሰነድ ላይ ውይይት በማድረግ ርዕሰ መስተዳድሩ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በንቅናቄው ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣ የቢሮ ሃላፊዎች፣ የዞንና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የመዋቅሩ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
የማር ምርት እጅግ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በጎምቦራ ወረዳ በንብ ማነብ ስራ የተሠማሩ አርሶአደሮች ተናገሩ
ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሰ የግብርና ልማት ላይ አደጋ እንዳያስከትል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለጸ
የገጠር ኮሪደር ኤኒሼቲቭ የገጠርሪቱን ኢትዮጵያ አኗኗር ዘይቤ በእጅጉ የሚያዘምን መሆኑ ተገለጸ