ተጠባቂው የኤልክላሲኮ ደርቢ በባርሴሎና አሸናፊነት ተጠናቀቀ
በስፔን ላሊጋ 11ኛ ሳምንት በሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና መኻከል የተካሄደው የኤልክላሲኮ ደርቢ በባርሴሎና 4ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ለባርሴሎና ከዕረፍት መልስ የተገኙትን የማሸነፊያ ግቦች ሮበርት ሊቫንዶውስኪ ሁለት ሲያስቆጥር ላሚን ያማል እና ራፊንያ ቀሪ ግቦችን ከመረብ አሳርፈዋል።
ሮበርት ሊቫንዶውስኪ በላሊጋው ያስቆጠራቸውን ግቦች 14 አድርሷል።
ላሚን ያማል በበኩሉ በኤልክላሲኮ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል።
በውድድር ዓመቱ 10ኛ ድሉን ያሳካው ባርሴሎና ነጥቡን 30 በማድረስ መሪነቱን አጠናክሯል።
ሪያል ማድሪድ በላሊጋው ከ42 ጨዋታዎች በኋላ ያለመሸነፍ ጉዞው በብሉግራናዎቹ ተገቷል።
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
ማርቲን ኦዴጋርድ ለአንድ ወር ያህል ከሜዳ ይርቃል
ሞሮኮ አሜሪካን በማሸነፍ ለግማሽ ፍፃሜ ደረሰች
ኤርሊንግ ሀላንድ 50 ጎሎች ላይ ፈጥኖ የደረሰ ተጫዋች ሆነ