በጀርመን ፍራንክፈርት በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሀዊ ፈይሳ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች።
አትሌቷ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ25 ሴኮንድ ፈጅቶባታል።
በወንዶች ማራቶን አትሌት ጎሳ አንበሉ 2ኛ እንዲሁም አትሌት ሌንጮ ተስፋዬ 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል።
በሌላ በኩል አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በቫሌንሽያ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን አዲስ የዓለም ክብረወሰን በማስመዝገብ አሸንፏል።
አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ግማሽ ማራቶኑን 57 ደቂቃ ከ30 ሴኮንድ በማጠናቀቅ ነው አዲስ የዓለም ክብረወሰን ያስመዘገበው።
በሴቶች ግማሽ ማራቶን አትሌት ፎቴን ተስፋዬ 2ኛ፣እጅጋየሁ ታዬ 4ኛ እና ፅጌ ገብረሰላማ 5ኛ በመሆን አጠናቀዋል።
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች