ሠላምን በሠላም ጊዜ እንደሚሠራ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 02/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሠላምን በሠላም ጊዜ መስራት እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በደቡብ ኢትየጵያ ክልል ከፍተኛ የፀጥታ ምክር ቤት አመራሮች፣ የጌዴኦ ዞንና የዲላ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላትና ባለድረሻዎች በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ዙሪያ የውይይት መድረክ በዲላ ከተማ አካሂደዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ ለሚሠሩ ሥራዎች ሠላም ወሳኝ በመሆኑ ሠላምን በሠላም ጊዜ በመሥራት የሀገራችንና የአካባቢያችንን ደህንነት ማሰጠብቀ አለብን ብለዋል።
አክለውም በዞኑ ህገ ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴ ከመከላከልና የአካባቢውን ሠላም ከማስጠበቅ አኳያ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን አንስተው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ፍትሀዊ እንዲሆን የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት መሥራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የጌዴኦ ዞንና የዲላ ከተማ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊዎች አቶ ሽብሩ ሚጁና አቶ አለማየሁ ጂግሶ የፀጥታው ምክርቤት ሠነድ ያቀረቡ ሲሆን፥ ሠላም ሕዝባዊ መሠረት እንዲይዝ ከማድረግ አኳያ ወንጀሎችን መከላከል፣ ህገወጥ ንግድ ቁጥጥርና ሌሎችንም በርካታ ተግባራት በቀጣይነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅተው በትኩረት አንደሚሠሩ በሪፖርታቸው አንስተዋል።
አክለውም ኃላፊዎቹ አካቢውን በማስጠበቅና የውስጥ ሚሊሻ በማጠናከር የህገወጥ ቤንዚል ንግድና ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል ከፍትህ፣ ከፀጥታና ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን አስታውሰው፥ በቀጣይም በትኩረት እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።
የደቡብ ኢትየጵያ ክልል የሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አቤኔዘር ተፈራ በበኩላቸው፥ አደረጃጀትን በአግባቡ በመጠቀም የውስጥ ኃይልን በማጠናከር የሠላም ግንበታውን ተግባራዊ ለማድረግ የወረዱ አሠራሮችና ፕላት ፎርሞችን በአግባቡ መተግበር ይጠበቃል ብለዋል።
ከተሳታፊዎች የከፍተኛ መከላከያ አመራር ብርጋዲየር ጄኔራል አስፋው ማመጫ አስፋው ማመጫ በሀገራችን የተጀመረውን ልማት አስጠብቆ ለማስቀጠል ሀገራዊ ራዕይና ተልኮ ለማሳካት በሰላሙ ጉዳይ ከማህረሰባችን ጋር መሥራት ይጠይቃል በማለት የሀገራችንን ሶሺዮ-ኢኮኖሚ ሊጎዱ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል።
የህገ ወጥ ንግድ የሀገርን ኢኮኖሚ ከሚጎዱ ነገሮች አንድ በመሆኑ በተደረገው ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር መቀነሱን ጠቁመው፥ በቀጣይም ኮንትሮባንድ የሚፀየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር የግንዛቤ ሥራዎችን በትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን አጋርተዋል።
ዘጋቢ: ፅጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያዎችን

More Stories
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሴንተር ፎር ኢምፓወርመንት ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በጎፋ ዞን ለሲቪክ ማህበራት ስልጠና ሰጠ
የሃይማኖት ተቋማት ፅንፈኝነትን፣ አክራርነትንና ከፋፋይ አጀንዳዎችን በመጠየፍ ሰላምና አንድነትን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተገለጸ
በኩታ ገጠም እርሻ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች የአርሶአደሩን ኑሮ ለማሻሻል አይነተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ