ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ እግር ኳስ ተጫዋች ሆነ

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ እግር ኳስ ተጫዋች ሆነ

ፖርቹጋላዊው ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ2024 ከፍተኛ ተከፋይ የእግር ኳስ ተጫዋች መሆኑን የፎርብስ ጋዜጣ አስነብቧል።

በአሁኑ ወቅት ለሳውዲ አረቢያ አልናስር እየተጫወተ የሚገኘው ሮናልዶ በ2024 የውድድር ዘመን ከታክስ በፊት 285 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን ጋዜጣው አስነብቧል።

ተጫዋቹ ከዓመታዊው የደሞዝ እና ስፖንሰርሺፕ ስምምነት ገቢ በማግኘት ቀዳሚውን ደረጃ መያዙ ተነስቷል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶን በመከተል ሊዮኔል ሜሲ በ124 ሚሊዮን ዩሮ ዓመታዊ ገቢ 2ኛ ደረጃን ሲይዝ ኔይማር በ101 ሚልዮን ዩሮ 3ኛ ሆኗል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2023 የውድድር ዘመንም 260 ሚሊዮን ዶላር በማግኘት ከዓለም ቀዳሚው እንደነበር አይዘነጋም።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ