በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ እና አርሰናል 2 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።
ኤርሊንግ ሃላንድ እና ጆን ስቶንስ የማንቸስተር ሲቲን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ሪካርዶ ካላፊዎሪ እና ጋብርኤል ማጋሌሽ ለአርሰናል አስቆጥረዋል።
በጨዋታው የአርሰናሉ ተጫዋች ሊያንድሮ ትሮሳርድ ጨዋታን በማዘግየት በሚል ከዕረፍት በፊት በሁለት ቢጫ (በቀይ ካርድ) ከሜዳ ተወግዷል።
ኤርሊንግ ሃላንድ ለማንቸስተር ሲቲ በ105 ጨዋታዎች 100ኛ ጎሉን ሲያስቆጥር በጥቂት ጨዋታዎች 100 ጎሎችን በማስቆጠር ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር ተጋርቷል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ሆዜ ሞሪንሆ እና ዲዬጎ ሲምዮኔ ከ12 ዓመታት በኋላ በማድሪድ ደርቢ ይፋለማሉ
የሪያል ማድሪድ ትኩረት በ ማንችስተር ዩናይትድ ታዳጊ ጄጄ ጋብርኤል ላይ
“ከማክስ ዶውማን ጋር መስራት ትልቅ ደስታ ነው” ሚኬል አርቴታ