በአንድ ጀምበር ችግኝ የመትከል መርሃ-ግብር በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ ቆረር ቀበሌ እየተከናወነ ነው

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) እንደ ሀገር በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ-ግብር በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ ቆረር ቀበሌ እየተከናወነ ነው።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ፣ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና ወረዳ አመራሮች እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፡ ሚፍታህ ጀማል – ከወልቂጤ ጣቢያችን