በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር የክልል አመራሮች የመንግስት ሥራ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር የክልል አመራሮች የመንግስት ሥራ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 08/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር የክልል አመራሮች የመንግስት ሥራ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በጂንካ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በሁሉም ዘርፍ ቃልን በተግባር ማረጋገጥ በሚል መርህ ቃል በክላስተሩ የሚገኙ አመራሮች ምዘና እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡

መድረኩን የመሩት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ፥ አመራሩ ዲስፕሊንን በመጠበቅ የሚፈጠሩ ቀውሶችን በብቃት በመምራት ጠንካራ ሀገረመንግስት ለመገንባት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡

በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን በመጠቀም የሕዝብን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ፓርቲው ሰው ተኮር ሥራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡

አመራሩ በየዘርፉ በብቃት በማቀድና በማስፈፀም ለማህበረሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያበረከቱ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ አሳስበዋል፡፡

በማህበራዊ ክላስተር ቢሮዎች የተመዘገቡ ውጤቶችና የነበሩ ውስንነቶች በሚታረሙበት አቅጣጫ ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን