በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአረንጓዴ አሻራ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት በሳንኩራ ወረዳ ረግዲና ቆሬ ቀበሌ እየተካሄደ ነው፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፣ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም በርካታ በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 ሚሊየን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደረጃ ደግሞ 5 ሚሊየን ችግኞችን በአንድ ቀን የመትከል መርሃ-ግብር ሚሊዮኖችን በማሳተፍ እየተካሄደ ነው።

ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ