የመንግስት በጀት ለታለመለት ዓላማ በአግባቡ ሊውል እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኦሞ ዞን የበና ፀማይ ወረዳ በ4ተኛ ዙር 6ተኛ ዓመት 23ተኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2017 የመንግስት ስራ ማስፈጸሚያ 226 ሚሊዮን 843 ሺህ 681 ብር በጀት አጽድቋል፡፡
የበና ፀማይ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ጋልቦ ጉሜ የማህበረሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተው፥ የ2017 የፀደቀው በጀት ትኩረት ለሚሹ ዋና ዋና የልማት ግቦች ብቻ ማዋል እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዋናው አፈ ጉባኤው አያያዘው እንደገለጹት፥ ልማት ያለ ማህበረሰብ ተሳትፎ ማሳካት እንደማይቻል ጠቁመው፥ በበጀት አመቱ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ማህበረሰቡ ለታቀደው የልማት ሥራ የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
በበጀት አመቱ የምክር ቤቱ አባላት ያነሷቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በየደረጃው ለመፈታት እንደሚሰራ ያረጋገጡት የበና ፀማይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሐንስ ጋርሾ በተዋረድ ያሉ የህዝብ ምክር ቤቶች ህዝቡን የማስተባበር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ምክር ቤቱ ለ2017 በጀት ዓመት ሥራ ማስፈፀሚያ 226 ሚልዮን 843 ሺ 681 ብር አድርጎ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
ዋና አስተዳዳሪ በተጓደሉ የካቢኔ አባላትና የምክር ቤቱን ቋሚ ኮሚቴ አቅርበው በምክር በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡
ዘጋቢ፡ አርሻል አራቦ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ
መስራት እየቻሉ የገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግሮች ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ቀላል አለመሆኑ ተገለጸ
በስልጤ ልማት ማህበር ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰበሰቡ የአካባቢው ተወላጆች በዞኑ በሚገኙ የላንፉሮ ወረዳና ጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኞችን ተክለዋል ።