ዥንጉርጉርነት
በፈረኦን ደበበ
አፍሪካን እንደ አህጉር በምንመለከትበት ጊዜ የምናገኘው ገጽታ አስገራሚ ነው፡፡ መቻቻል የመኖሩን ያህል ውጥረቶች ይስተዋላል፡፡ የልዩነት ኃይሎች የመኖራቸውን ያህል የአንድነትና እንዲሁም መንገዱ ቢለያይም ለብልጽግና ማሰባቸው ተስፋ ይሰጣል፡፡ “የሰው ልጅ ህይወት ውጣ ውረድ የተሞላበት ነው” ከሚለው እሳቤ አንጻር ወስደን “ጭቅጭቅ በቤተሰብ መሀልም ይከሰታል” ከሚለው ጋር እንዳናገናኝ ግን አሁን በሱዳን እንደሚታየው ሀገርና ህዝብን በቦንብ ናዳ መፍጀቱ ያሳዝናል፡፡
እንደ ሩዋንዳና ሞሮኮ የመሳሰሉና በውስጣቸው ጸጥ ረጭ ያለው ህይወት በሠሀራ በረሃ ሙቀትና ቃጠሎ ከሚያጣጥሙት ምዕራብ አፍሪካዊያን ጋር እጅግ ይቃረናል ምክንያቱም የአሸባሪዎች ጥቃት ታክሎበትና በኃያላን ሽኩቻ ምስቅልቅል ሁኔታ ስለተፈጠረ፡፡ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶና ኒጀር እንዲሁም የኋላ ኋላ ሴኔጋልን ያካተተው ይህ ጥምረት ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት በተደጋጋሚ ህጋዊ ያልሆኑ የመንግሥት ለውጦችን አካሂደዋል፡፡
ህብረታቸውንም ለማስጠበቅ ሲባል የአካባቢው ምጣኔ ሀብታዊ ማህበረሰብ ተብሎ ከሚጠራው “ኢኮዋስ” ጋር ወደ ፍጥጫ ገብተዋል፡፡ በሰሜኑ ያለውን ውጣ ውረድ ከማንሳታችን በፊት ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ቀጠና ጎራ ስንል በታሪክ ረጅም ጊዜ የወሰደውን የዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ጦርነትን እንመለከታለን በውስጡ እንደ ሩዋንዳ ያሉ ጎረቤት ሀገራት እጅ ሁሉ ገብቶበት ሰዎችን ለሞትና መፈናቀል ስለዳረገ፡፡ በአካባቢው እንደ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ቶጎ እና ሌሎች ድምጻቸው እንኳን ሳይሰማ የሚኖሩትን ወስደን ለመመልከት ዩጋንዳን መጥራትም የግድ ይላል ምክንያቱም ባለው የፖለቲካ ትኩሳት መነሻ ጥላቻው ብቅ ጥልቅ እያለ ስለሆነ፡፡ በቅርቡ በኬኒያ የተካሄደውን ሰፊ የህዝባዊ ተቃውሞና ያመጣውን ለውጥ የተመለከቱት የሀገሪቱ ዜጎች ለተመሳሳይ ዓላማ ባለፈው ሳምንት ወደ አደባባይ ቢወጡም የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በወሰዷቸው እርምጃዎች ሀሳባቸውን ለመቀየር ተገደዋል፡፡
በአህጉሪቱ ለተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ችግሮች የበለጠ ተጋላጭ ተብሎ የሚታወቀውን የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና አንስተን ለማለፍ ብንፈልግ ሱዳንና ደቡብ ሱዳንን እንመለከታለን፡፡ ሁኔታቸው በአህጉሪቱ ረጅም ጊዜ ከወሰደውና ሁለቱ ህዝቦችን ለእርስ በርስ ግጭት ከዳረገበት አጋጣሚ እምብዛም መሻሻል ባለማሳየቱ፡፡ በሱዳን ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረው ህዝባዊ ተቃውሞ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርን ከሥልጣን በማስወገድ ብቻ ይጠናቀቃል ተብሎ ነበር፡፡ ሆኖም ከዚሁ የባሰ ችግር አስከትሏል ምክንያቱም ወታደሩ ወደ ፖለቲካው በመግባቱ የለውጥ ተስፋ ስለጨለመ፡፡
የዜጋውን ጥያቄዎች በአግባቡ በመመለስ ሀገሪቱን ማረጋጋት ያቃታቸው ወታደራዊ ክንፎች ኋላ ኋላ የገቡበት የእርስ በርስ ጥላቻም አሁን ለተፈጠረው ሞት፣ መፈናቀልና እንግልት ሲዳርግ በደቡብ ሱዳን ያለው ሁኔታም በተመሳሳይ አሳሳቢ ነው በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ችግሮች ስለተጠናወታት፡፡ በርካታ በአህጉሪቱ አዲስ የተከሰቱ ግጭቶችና ችግሮች የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት እንዲሁም ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት በሩሲያና ዩክሬን መካከል የተጀመረውን ጦርነት ተከትሎ በተፈጠረው የሸመታ ዕቃዎች ዋጋ ውድነት ሲሆን ይህ ከአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች ጋርም ተገናኝቷል፡፡ በጉልህ ከታዩ ቀጠናዎች መካከል የሰሜኑ የአህጉሪቱ ክፍል አንዱ ሲሆን ችግሩ በአካባቢው ካለው የስደተኞች ጫና ጋርም ይገናኛል ምክንያቱም ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚጠቀሙበት መንገድ 87 በመቶ ለሚሆኑት ጥፋቶች ተጠያቂ የሆኑት የፖሊስ ሃይሎች መሆናቸው ታውቋል። ይህ የጋዜጠኞችን አያያዝ በተመለከተ በሕግ አስከባሪ አካላት ውስጥ ያሉ የስርዓት ችግሮችን ያሳያል። የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ (NISA) በግምት 9 በመቶ ከሚሆኑት ጥቃቶች ጋር የተሳተፈ ሲሆን ይህም የመንግስት ተዋናዮች የሚዲያ ነፃነትን በማፈን ረገድ ያላቸውን ሚና ይጠቁማል።
ሪፖርቱ ጋዜጠኛ እና የሶማሌ ኬብል ቲቪ ዳይሬክተር አብዲፈታህ ሙአሊም ኑር እና ሌሎችም ላይ የተፈጸመውን አሳዛኝ ሞት አጉልቶ ያሳያል። ጋዜጠኛው እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 16 2023 በሞቃዲሾ ብሉ-ስኪ ሬስቶራንት ላይ በተፈጸመ እንደመሆኑ፡፡ አደገኛ የሆነውን ይህንን አዝማሚያ የተረዱት የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የኋላ ኋላ ባደረጉት የገንዘብና የተለያዩ ድጋፎች መጠነኛ መረጋጋት ቢኖርም እንደ ቱኒዚያ ባሉ ሀገራት የሚታየውን ችግር ግን ማስቆም አልተቻለም። ችግሩን ይቀርፋል በሚል የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ከይስ ሰይድ ያዘጋጁት ህገ-መንግሥትም ለህዝቡ ሠላምና ፍትህ አላጎናጸፈም በሚል ወቀሳ እየፈጠረባቸው ይገኛል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተከሰተው የዕቃዎች ዋጋ ውድነት በተጨማሪ በፍልስጤምና እሥራኤል ጦርነት ምክንያት ምጣኔ ሀብቷ የተጎዳባት ግብጽና ጎረቤቷ ሊቢያም ቢሆን እራሳቸውን በአግባቡ ማቋቋም የተሳናቸው ሆነዋል ምንም እንኳን ስደተኞችን ለመከላከል ሲባል ከአውሮፓ ህብረት ብዙ ገንዘብ ቢያገኙም፡፡ የዓለም ብሎም በሁሉም የአህጉሪቱ አካባቢዎች ጎልቶ በሚታየው የዕቃዎች ዋጋ ውድነት ተጎጂ የሆነው ሌላው ቀጠና የደቡቡ ሲሆን ይህ ደግሞ ጥርስ አግጥጦ የወጣው በደቡብ አፍሪካ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት ከተከሰተው የዕቃዎች ዋጋ ውድነት በተጨማሪ ፋብሪካዎቿ በኃይል እጥረት መነሻ ሥራ አቁመው የቆዩባት ሀገር ህዝባዊ ተቃውሞዎችንም ስታስተናግድ ቆይታለች፡፡ ውጣ ውረድ በነገሰበት ሁኔታ የተካሄደው ሌላው ሀገራዊ ሁነት በቅርቡ የተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ሲሆን ይህም ሥልጣን ይዞ ለረጅም ዓመታት ሀገሪቱን የመራውን “አፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ” የተባለው ገዢ ፓርቲ የበላይነቱን እንዲያጣም አድርጎታል በመንግሥት ምሥረታ ወቅት የተፈጠረውን ውጣ ውረድ እንኳን ባንቆጥር፡፡
በገንዘብ ምንዛሬ እና ባለባት ምጣኔ ሀብት ቀውስ ከምትታወቀው ዝምባብዌ በስተቀር ሌሎች የአካባቢው ሀገራት ስማቸው እየተነሳ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ዕድገትና ልማትን ለማምጣት የሚደረጉ ጥረቶችም ይበል የሚያሰኙ ናቸው፡፡ ሠላማቸውን አስጠብቀው ለህዝባቸው ኑሮ መሻሻል ጥረት የሚያደርጉ ሀገራትን እና ከችግሮች ብዛት የተነሳ ውጣ ውረዶችን የሚያልፉ ሀገራትን ስናነጻፅር የምናገኛት ሌላኛዋ ሀገር ኬኒያ ናት። በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው ምጣኔ ሀብት ችግር ምክንያት ዜጎች በተቃውሞ የቆዩባት ሀገር በመሆኗ በርካታ ፖለቲካዊ ችግሮች እያለፈች ነው የምትገኘው፡፡
ቀውሱ ተባብሶ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በጠባብ ልዩነት ወደ ሥልጣን የመጡትን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶን ጭምር ከመንበራቸው አነቃንቋል ምንም እንኳን የኋላ ኋላ ተቃዋሚ አባላትን ሁሉ በካቢኔያቸው ውስጥ በማካተት ሁኔታውን ለማብረድ ቢሞክሩም፡፡ መንግሥት አግባብ ከሆነው መንገድ ውጭ ግብር ጨምሮብናል በሚል ቅሬታ ወደ አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች ማሻሻያ ከተደረገበትና ህጉ ከተሠረዘ በኋላም ተቃውሟቸውን መቀጠላቸው አስገራሚ ሆኗል በሀገሪቱ ሙስና እንዳለና /የሀገሪቱ ሃብት/ በአግባቡ በሥራ ላይ እንደማይውል በመጠቆም፡፡
ከእነዚህ ሀገራት ውጪ በአፍሪካ በህዝብ ብዛት ተጠቃሽ የሆኑት ኢትዮጵያና ናይጀሪያም ከቀውስ የተረፉ አልሆኑም ምንም እንኳን ችግሮች እንደየሀገራቱ ቢለያዩም፡፡ ኢትዮጵያ የተከሰተውን የፖለቲካ ቅራኔ በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት መነሳቷና ናይጄሪያም ከኑሮ ውድነት ችግሮች ጋር ተያይዞ የተነሳውን ተቃውሞ በልማታዊ መንገድ ለመመለስ መነሳሳቷ ተጠቃሽ ያደርጋቸዋል፡፡ ሶማሊያም የተረጋጋች እንድትሆን የሚደረግላት ድጋፍ እንዲሁ፡፡
More Stories
“ሳንቲም ሲጥሉልኝ አመስግኜ ነው የምመልሰው” – ወጣት ማህቶት በለጠ
“ጥበብ ነገሮችን በተለየ መንገድ ማየት መቻል ነው” – ተወዛዋዥ ተስፋ ጽዮን ንጉሴ
ትኩረት ሊሰጠው ይገባል!