ማንቸስተር ዩናይትድ ማቲያስ ዴሊትን ለማስፈረም ተስማማ

ማንቸስተር ዩናይትድ ማቲያስ ዴሊትን ለማስፈረም ተስማማ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 04/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የእንግሊዙ እግርኳስ ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ ማቲያስ ዴሊትን ለማስፈረም ከባየርሙኒክ ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል።

ኔዘርላንዳዊው የመሃል ስፍራ ተከላካይ ወደ 50 ሚሊዮን ዩሮ የሚጠጋ የዝውውር ዋጋ ወጥቶበትና ተጨማሪ 12 ወራትን ያካተተ የ5 ዓመት ውል በመፈረም ማንቸስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ መደረሱን ዘአትሌቲክ አስነብቧል።

ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በተያያዘ የቀኝ መስመር ተከላካያቸው አሮን ዋን ቢሳካ ወደ ምስራቅ ለንደኑ እግርኳስ ክለብ ዌስትሃም ዩናይትድ ለመዛወር መስማማቱ ተነግሯል።

በአንፃሩ ማንቸስተር ዩናይትድ ሌላኛውን የባየርን ሙኒክ ተከላካይ ኖስር ማዝራውን የቢሳካ ምትክ አድርጎ ለማስፈረም ከባቫሪያኑ ክለብ ጋር መስማማቱ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ቶትንሃም ሆትስፐርስ የዶሚኒክ ሶላንኬን ዝውውር ማጠናቀቁ ይፋ ሆኗል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ የ26 ዓመቱን እንግሊዛዊ አጥቂ ከበርንማውዝ ለማዛወር 65 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣ ሲሆን የቼልሲው ኮባሃም አካዳሚ ፍሬ የሆነው ሶላንኬ በነጭ ለባሾች ቤት እ.ኤ.አ እስከ 2030 ድረስ የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል።

የቀድሞ የአርሰናልና የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች የነበረው አሌክሲስ ሳንቼዝ ወደ ሌላኛው የቀድሞ ክለብ ዩዲኒዚ በነፃ ዝውውር አቅንቷል።

የ35 ዓመቱ ቺሊያዊው የፊት መስመር ተጫዋች በጣሊያኑ ክለብ የአንድ ዓመት ውል መፈረሙ ታውቋል

በሙሉቀን ባሳ