ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት ሁለት የፍፃሜ ውድድሮች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ
ከሰዓታት በፊት በ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ የመጀመሪያዋን የወርቅ ሜዳልያ በወንዶች ማራቶን ማሸነፍ የቻለችው ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት የወንዶች 5 ሺህ ሜትርና የሴቶች 1ሺህ 500 የፍፃሜ ሩጫ ውድድር ዛሬ ምሽት ይካሄዳል።
ምሽት 2 ሰዓት ከ50 ላይ በሚካሄደው የወንዶች 5ሺህ ሜትር ሩጫ ፍፃሜ አትሌት ሃጎስ አረጋዊ፣ቢኒያም መሃሪና አዲሱ ይሁኔ በኢትዮጵያ በኩል ተወዳዳሪዎች ናቸው።
በርቀቱ ሁለተኛው የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነው አትሌት ሃጎስ ገብረ ህይወት በዘንድሮው ዓመት በዓለም አገር አቋራጭ 5 ኪሎሜትር እንዲሁም በ13ኛው የመላ አፍሪካ ስፖርቶች ሻምፒዮና በ5ሺህ ሜትር ለሃገሩ የወርቅ ሜዳልያ ማስገኘቱ ይታወቃል።
ታዳጊው አትሌት ቢኒያም መሃሪ በበኩሉ በ5 ሺህ ሜትር 12 ደቂቃ ከ54 ሴኮንድ ከ10 ማይክሮሴኮንድ የሆነ የግሉ ፈጣን ሰዓት አለው።
የዓለም ከ20 ዓመት በታች አሸናፊው አዲሱ ይሁኔ ደግሞ የግሉ ፈጣን ሰዓት 12 ደቂቃ ከ49 ሴኮንድ ከ65 ማይክሮ ሴኮንድ ነው።
አትሌት ምሩፅ ይፍጠር፣አትሌት ሚሊዮን ወልዴና አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በኦሎምፒክ 5ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ለኢትዮጵያ እስከአሁን የወርቅ ሜዳልያ ያስገኙ አትሌቶች ናቸው።
የሴቶች 1ሺህ 500 ሜትር ፍፃሜ የሩጫ ወድድር ምሽት 3 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ላይ ይደረጋል።
በውድድሩ በኢትዮጵያ በኩል አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬና ድርቤ ወልተጂ ለሜዳልያው ይፋለማሉ።
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሮድሪጎ ቤንታንኩር ከእግር ኳስ ጨዋታዎች ታገደ
በቀቤና ልዩ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ 5ተኛ አመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ ማህበረሰብ አቀፍ የማስ ስፖርት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ጤናማና ንቁ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ