ሦስት ኢትዮጵያዊ አትሌቶች በዛሬው የግማሽ ፍፃሜ ውድድራቸውን ያካሂዳሉ
በ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍፃሜ ሩጫ ሦስት ኢትዮጵያዊ አትሌቶች ዛሬ ምሽት ይወዳደራሉ።
ምሽት 2 ሰዓት ከ35 ላይ በሚካሄደው የግማሽ ፍፃሜ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣ አትሌት ደርቤ ወልተጂና አትሌት ብርቄ ሃየሎም በኢትዮጵያ በኩል ተወዳዳሪዎች ናቸው።
ቅዳሜ ምሽት 3 ሰዓት ከ35 ላይ ለሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር ለማለፍ አትሌት ብርቄ ሐየሎም በመጀመሪያው ምድብ እንዲሁም አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬና ድርቤ ወልተጂ በሁለተኛው ምድብ ተደልድለው የግማሽ ፍፃሜ ውድድራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ማንቸስተር ሲቲ እና አርሰናል በአቻ ውጤት ተለያዩ
የእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ አዲሱ የውድድር ዘመን ዛሬ ምሽት ይጀምራል
ማንቸስተር ሲቲ የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫን አሸነፈ