ኖቫክ ጆኮቪች ካርሎስ አልካሬዝን በማሸነፍ በኦሎምፒክ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አገኘ
በፈረንሳይ አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ በሚገኘው 33ኛ የፓሪስ ኦሎምፒክ በተካሄደው የነጠላ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ሰርቢያዊው ኖቫክ ጆኮቪች ስፔናዊውን ካርሎስ አልካሬዝን በማሸነፍ በኦሎምፒክ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ማግኘት ችሏል።
የ24 ጊዜ የግራንድ ስላም አሸናፊው ኖቫክ ጆኮቪች፥ የዓለም ቁጥር ሶስት የሜዳ ቴኒስ ተወዳዳሪውን ካርሎስ አልካሬዝን በሁለቱም ዙሮች 7ለ6 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው የወርቅ ሜዳልያው ባለቤት መሆን የቻለው።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ክብረወሰኖች የሚከተሉት ተዓምረኛ
አትሌት መሠረት ደፋር የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ሽልማት ተበረከተላት
ማርቲን ኦዴጋርድ ለአንድ ወር ያህል ከሜዳ ይርቃል