በ1500 ሜትር ማጣሪያ ሁለት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፉ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 26/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በ1500 ሜትር በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር አትሌት ኤርሚያስ ግርማ እና አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ማጣሪያውን በማለፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መድረስ ችለዋል።
በምድብ ሁለት የተወዳደረው አትሌት ኤርሚያስ ግርማ 3:35.21 በሆነ ሰዓት በመግባት ማጣሪያውን በአንደኝነት በማጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።
በምድብ ሦስት የተወዳደረው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።
በመጀመሪያው ምድብ ተወዳድሮ የነበረው አትሌት አብዲሳ ፈይሳ ቀጣዩን ዙር መቀላቀል ሳይችል ቀርቷል።
የ1500ሜ ወንዶች ግማሽ ፍፃሜ ውድድር የፊታችን ዕሑድ ምሽት 4:10 ሰዓት የሚደረግ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ማንቸስተር ሲቲ በአዲሱ የውድድር ዓመት 2ኛ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል
ጄሚ ቫርዲ ወደ ጣሊያን ሴሪኣ ሊያቀና ነው