በ800 ሜትር ሴቶች አትሌት ወርቅነሽ መለሰ እና ፅጌ ድጉማ ወደ ፍፃሜው አለፉ
በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ በ800 ሜትር ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ የተወዳደሩት አትሌት ወርቅነሽ መለሰ እና አትሌት ፅጌ ድጉማ ወደ ፍፃሜው አልፈዋል።
በመጀመሪያው ምድብ የግማሽ ፍፃሜ ውድድሯን ያከናወነችው አትሌት ወርቅነሽ መሰለ 2ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።
በሁለተኛው ምድብ ወደ ፍፃሜው ለማለፍ የተወዳደረችው አትሌት ፅጌ ድጉማ አንደኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች።
የሴቶች 800 ሜትር ፍፃሜ ውድድር ነገ ምሽት 4 ሰዓት ከ45 ላይ የሚደረግ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ማንቸስተር ሲቲ እና አርሰናል በአቻ ውጤት ተለያዩ
የእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ አዲሱ የውድድር ዘመን ዛሬ ምሽት ይጀምራል
ማንቸስተር ሲቲ የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫን አሸነፈ