ምሽቱን በተካሄዱ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ድል ቀንቷቸዋል
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ከሜዳው ውጪ ፒኤችዲን የገጠመው ባርሴሎና 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ከአራት ዓመታት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊጉ ሩብ ፍፃሜ ለደረሰው ባርሴሎና የማሸነፊያ ጎሎችን ራፊንሃ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ተቀይሮ የገባው አንድሬ ክርስቲያንሰን ቀሪዋን ጎል አስቆጥሯል።
ከ27 ጨዋታ በኋላ ሽንፈትን ላስተናገደው ፒኤስጂ ደግሞ ኦስማን ዴምብሌ እና ቪቲኒሃ የማስተዛዘኛ ጎሎችን አስቆጥረዋል።
ብራዚላዊው ራፍንሃ በእግርኳስ ተጫዋችነት ዘመኑ በአውሮፓ ሻምፒዮንስሊግ የመጀመሪያውን እና ሁለተኛ ጎሉን ያስቆጠረ ሲሆን ከሊድስ ዩናይትድ ባርሴሎናን ከተቀላቀለ ወዲህ በአንድ ጨዋታ ሁለት ጎል ሲያስቆጥር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
በሌላ በኩል አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው ቦሩሲያ ዶርትሙንድን 2ለ1 ረቷል።
ሮድሪጎ ዴፓውል እና ሳሙኤል ሊኖ ለስፔኑ ክለብ የማሸነፊያ ጎሎችን ሲያስቆሩ ሴባስቲያን ሃለር ተቀይሮ ገብቶ ክለቡ በጠባብ ውጤት እንዲሸነፍ ያስቻለችውን ጎል አስቆጥሯል።
አይቮሪኮስታዊው አጥቂ ሴባስቲያን ሃለር በ13 የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ 12ኛ ጎሉን ነው ማስቆጠር የቻለው።
ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በተካሄዱት 4 የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች በድምሩ 18 ጎሎች ተቆጥረዋል።
የመልስ ጨዋታዎች የፊታችን ማክሰኞ እና ረቡዕ ይከናወናሉ
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ያለምንም ችግር እንዲካሄድ በቂ ዝግጅት መደረጉን የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ገለፁ
ዳራማሎ ደንዳሾ ስፖርት ክለብ ባስኬት ቡናን በማሸነፍ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ ሆነ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ለፍፃሜ ያለፉ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል