ጆሿ ዚርኪዜ በሮማ ይፈለጋል

ጆሿ ዚርኪዜ በሮማ ይፈለጋል

የጣሊያኑ ክለብ ሮማ የማንቸስተር ዩናይትዱን የፊት መስመር ተጫዋች ጆሿ ዚርኪዜን የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል።

በአሰልጣኝ ጂያንፔሮ ጋስፔሪኒ የሚመራው ሮማ ኔዘርላንዳዊውን አጥቂ በጥር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በውሰት ካስፈረመው በኋላ ዝውውሩን ቋሚ የማድረግ ፍላጎት ማሳየቱን ስካይ ስፖርት አስነብቧል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቹ በጣሊያኑ ክለብ እንደሚፈለግ ቢያውቅም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ እያሳየ በሚገኘው እንቅስቃሴ ግን አሳልፎ የመስጠት ፍላጎት እንደሌለው ዘገባው ጠቁሟል።

የአሰልጣኝ ሩበን አሞሪሙ ቡድን ቤንጃሚን ሴስኮ እና ማቲያስ ኩንኛ መጎዳታቸውን ተከትሎ ባለፉት 3 ተከታታይ የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች መሰለፉ ይታወቃል።

ከሁለቱ ተጫዋቾች ጉዳት በተጨማሪም አማድ ዲያሎ እና ብሪያን ምቤሞ በቀጣይ ሳምንት ወደ አፍሪካ ዋንጫ የሚያመሩ በመሆናቸው ዚርኪዜ በጥር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቡን የመልቀቅ ዕድል ላይኖረው ይችላል ተብሏል።

ከ18 ወራት በፊት ከሌላኛው የጣሊያኑ ክለብ ቦሎኛ ወደ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ የተዛወረው የ24 ዓመቱ ጆሿ ዚርኪዜ እስካሁን ለቀያይ ሰይጣኖቹ 58 ጨዋታዎችን በማከናወን 8 ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል።

ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ