ኢንተር ሚላን የጣሊያን ሴሪአ ዋንጫን ለ2ዐኛ ጊዜ አሸናፊ መሆኑን አረጋገጠ
የጣሊያኑ እግር ኳስ ክለብ ኢንተር ሚላን የጣሊያን ሴሪአ ዋንጫን ለ20ኛ ጊዜ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።
ኢንተር ሚላን አሸናፊ መሆኑን ያረጋገጠው በሚላን ደርቢ (ደርቢ ዴላ ማዶኒና) ታሪካዊ ባላንጣውን ኤሲ ሚላንን 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፉ ነው።
በዚህም ሴሪአው ሊጠናቀቅ 5 የጨዋታ ሳምንታት እየቀረው ከተከታዩ ኤሲ ሚላን ጋር የ17 ነጥብ ልዩነት በመፈጠሩ ኢንተር ገና ከወዲሁ አሸናፊ መሆኑ ታውቋል።
ሴሪአው በ116 ዓመታት ታሪኩ የዋንጫ አሸናፊው በደርቢ ዴላማዶኒና ሲታወቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
አዘጋጅ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ያለምንም ችግር እንዲካሄድ በቂ ዝግጅት መደረጉን የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ገለፁ
ዳራማሎ ደንዳሾ ስፖርት ክለብ ባስኬት ቡናን በማሸነፍ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ ሆነ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ለፍፃሜ ያለፉ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል