ጋብርኤል ማርቲኔሊ በ5 ተከታታይ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያው የአርሰናል ተጫዋች ሆነ
ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ጋብርኤል ማርቲኔሊ በአምስት ተከታታይ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያው የአርሰናል ተጫዋች ሆኗል።
የእንግሊዙ ክለብ አርሰናል ትናንት ምሽት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 6ኛ ዙር ጨዋታ ወደ ቤልጂየም አምርቶ ክለብ ብሩጅን 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ በውድድሩ በዚህ ዓመት 6ኛ ተከታታይ ድሉን እንዲያስመዘግብ ያስቻሉትን የማሸነፊያ ግቦች ኖኒ ማዱዌኬ ሁለት ጎሎችን አከታትሎ ሲያስቆጥር ጋብርኤል ማርቲኔሊ በ56ኛው ደቂቃ ቀሪዋን ጎል አስገኝቷል።
ጋብርኤል ማርቲኔሊ መድፈኞቹ በሻምፒዮንስ ሊጉ አትሌቲክ ቢልባኦን፣ኦሊምፒያኮስን፣አትሌቲኮ ማድሪድን እና ባየርንሙኒክን በተከታታይ ሲያሸንፉ ጎል ማስቆጠሩ ይታወሳል።
የ24 ዓመቱ በሻምፒዮንስ ሊጉ አጠቃላይ በ24 ጨዋታዎች የ9 ጎሎች ባለቤት ነው።
በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሻምፒዮንስ ሊጉ በ5 ጎሎች 3ኛው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ጆሿ ዚርኪዜ በሮማ ይፈለጋል
አርሰናል በአስቶንቫላ ተሸነፈ
ኮቢ ሜይኑ ማንቸስተር ዩናይትድን መልቀቅ ይፈልጋል