የሊቨርፑሉ አጥቂ አሌግዛንደር ኢሳቅ በእግሩ ላይ የቀዶ ጥገና ህክምና እንደተደረገለት ተገልጿል።
የብሪታንያ የምንጊዜም ውዱ ፈራሚ ኢሳቅ ከቀናት በፊት ከቶትንሃም ጋር በተካሄደ ጨዋታ የእግር ስብራት ጉዳት ማስተናገዱ ይታወሳል።
ተጫዋቹ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በቁርጭምጭሚቱ አካባቢ የቀዶ ጥገና ህክምና እንደተደረገለት የመርሲሳይዱ ክለብ አሳውቋል።
ስዊድናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ለምን ያኽል ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ግን ሊቨርፑል አልገለፀም።
እንደ ስካይ ስፖርት መረጃ መሰረት አሌግዛንደር ኢሳቅ ለወራት ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ተጠቁሟል።
የ26 ዓመቱ ተጫዋች ለሊቨርፑል እስካሁን 16 ጨዋታዎችን አከናውኖ 3 ኳሶችን ከመረብ ጋር አዋህዷል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
የቀን 6፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም #ደሬቴድ ፡ቀጥታ ስርጭት #ዜና24 #ዜና #ደቡብቴቪ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር ምርጫ 5ኛ የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡የካቲት 07/2018 ዓ.ም