የኣሪ ዞን ስፖርት ምክር ቤት የምስረታ ጉባኤውን አካሄዷል

የኣሪ ዞን ስፖርት ምክር ቤት የምስረታ ጉባኤውን አካሄዷል

ሀዋሳ፡ የካቲት 09/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኣሪ ዞን ስፖርት ምክር ቤት የምስረታ ጉባኤውን አካሄዷል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አኮየ አጎ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት፤ ስፖርት ወዳጅነትን፣ አብሮነትንና ህብረትን የሚፈጥር ኩነትና በአለምም ሆነ በሀገራችን  ትልቁ የገቢ ማግኛ ዘርፍ ብሎም የዲፕሎማሲ መስክ በመሆኑ ዘርፉን ለማጠናከር በፋይናስ ለመደገፍ ምክርቤቱ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለው አስገንዝበዋል።

የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የስፖርት ምክር ቤቱ ስብሳቢ አቶ አብርሃም አታ በንግግራቸው ስፖርት ከመዝናኛነት ባለፈ የኢኮኖሚ መሠረት ነው ብለዋል።

የአሪ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ይሄነው ተስፋዬ በበኩላቸው ዞኑ በአዲስ መልክ ከተደራጀ ጀምሮ ቢሮው በርካታ ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው የስፖርት ሥራን ለማከናወን የስፖርት ምክር ቤት መመስረት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።

በመድረኩ መነሻ የሚሆን ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበት ሲሆን የተለያዩ ውሳኔዎችን በመወሰን ዞናዊ ስፖርታዊ ወድድር የካቲት 21/2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተወሰኖ ጉባኤው ተጠናቋል።

ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን