የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል
በኮትዲቯር አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ምሽት 5:00 በሚካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ ይጠናቀቃል።
በድንቅ ብቃት እየገሰገሰች የመጣችው ናይጀሪያ እና በተዓምር እና ዕድል ታጅባ ለዛሬው ቀን የደረሳቸው ኮትዲቯር ይገናኛሉ።
አሁን ባላት ወቅታዊ ብቃት ናይጀሪያ የማሸነፍ ዕድል አላት እየተባለ ቢሆንም ኮትዲቯር በደጋፊዎቿ ታግዛ ዋንጫን በማሸነፍ ሌላ ተዓምር ታሳያለች እያሉ ነው የኳስ አዋቂዎች።
የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጥራት እና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እየተካሄደ መሆኑ የበርካቶችን ትኩረት እንዲያኝ አድርጎታል።
ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ ያደረገችው አስተናጋጅ ሀገር ኮትዲቯር ልፋቷ መና እንዳልቀረ በርካቶች እየመሰከሩ ነው።
የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ በበርካታ ድንገቴዎችና አዳዲስ ክስተቶች መታጀቡ ልዩ መገለጫው ነው፡፡
አዘጋጅ: ጀማል የሱፍ
More Stories
ዳራማሎ ደንዳሾ ስፖርት ክለብ ባስኬት ቡናን በማሸነፍ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ ሆነ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ለፍፃሜ ያለፉ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል
ስፖርት የወንድማማችነት እና የልማት መጠናከር አንዱ ማሳያ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ