የቸሃ ወረዳ እና የእምድብር ከተማ ተወላጆች በ8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነቡት 5 የመማሪያ ክፍሎች ያሉት ብሎክ ተመርቆ ለአገልግሎት በቃ
ሀዋሳ፡ የካቲት 04/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጉራጌ ዞን በእምድብር ከተማ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ በውጭ ሀገር የሚኖሩ የቸሃ ወረዳ እና የእምድብር ከተማ ተወላጆች በመተባበር በ8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነቡት 5 መማሪያ ክፍሎች ያሉት ብሎክ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በቀጣይም በትምህርት ቤቱ በ120 ሚሊዮን ብር የማስፋፍያ ግንባታ ለማከናወን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በአቶ አንተነህ ፍቃዱ እና በጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ላጫ ጋሩማ የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል።
በጉራጌ ዞን ዘመናዊ ትምህርት ለዜጎች በመስጠት የመጀመሪያ የሆነው የእምድብር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ1945 ዓ.ም በትምህርት ፋና ወጊው በታላቁ አባ ፍራንሷ ማርቆስ አስተባባሪነት እንደተገነባ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ትምህርተ ቤቱ አንቱ የተባሉ በርካታ ምሁራኖችን በማፍራት ቀደምትና ባለውለታ እንደሆነ ይገለጻል።
በፕሮግራሙ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል