የሀገሪቱን የተፈጠሮ ሀብት ብቻ በመጠቀም የዜጎችን ኑሮ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚቻል ተገለፀ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለማህበራዊ ክላስተር የመንግስት ሰራተኞች እየተሰጠ ያለው ስልጠና እንደቀጠለ ነው።
በስልጠናው ላይ ጥናታዊ ሰነድ ያቀረቡት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ እንደገለፁት ስልጠናው ዜጎች መብትና ግዴታቸውን ለይተው ቀልጣፋ አገልግሎትን ከትህትና ጋር ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።
ስልጠናው የመንግስት ሰራተኛው የሀገሪቱን ፖሊሲና ስትራቴጂ በመረዳት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ።
ኢትዮጵያ ከራሷም አልፋ ለሌሎች የሚተርፍ ሀብት አላት ያሉት አቶ ሰላሙ ይሄን ሀብትና ፀጋ መለየትና መጠቀም የዜጎቿ ግዳታ ስለመሆኑም ጠቁመዋል ።
ባለፉት አመታት ኢትዮጵያ በርካታ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች እንደገጠሟት የጠቀሱት አቶ ሰላሙ ይሄን ጫና መቋቋም የሚችል ኢኮኖሚ መፍጠር በመቻሉ ጫናውን መቋቋም ስለመቻሉ አስታውሰዋል ።
የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በኢንዱስትሪና ማምረቻ፣ በቱሪዝምና አገልግሎት እንዲሁም ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለማስፋፋት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በወራቤ ከተማ እየተሰጠ ባለው ስልጠና የክልሉ የትምህርት፣ የጤና፣ የሴቶችና ህፃናት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሰራተኞች እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ : ጀማል የሱፍ
More Stories
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የግብርና ግብዓቶች አጠቃቀም ማሻሻልና ማዘመን እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
ጥራት ያለው ኮረሪማ ለገበያ ለማቅረብና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ትኩረት መደረጉን የአሪ ዞን ቡናና ቅመማቅመም ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የቡና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን አርሶ አደሮች ገለጹ