የማህበረሰብ ተሳትፎ በማሳደግ የህብረተሰቡን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል – የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ
ሀዋሳ፡ የካቲት 01/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማህበረሰብ ተሳትፎ በማሳደግ የህብረተሰቡን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
ቢሮው በአማራጭ የማህበረሰብ ተሳትፎ ዙሪያ ለባድርሻ አካላት ስልጠና በዳውሮ ዞን ማረቃ ወረዳ ተሰጥቷል።
በስልጠናዉ መድረኩ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሀይሌ ዘውዴ በበኩላቸው የማህበረሰብ ተሳትፎ በማሳደግ ጤናማና ጠንካራ ህብረተሰብ ለመፍጠር የጤና ሁኔታ ለማሻሻል ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀላፊው አክለውም የማህበረሰብ ተሳትፎ በክልሉ ለጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ተግባራዊነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ መኖሩን ገልፀዉ ህበረተሰቡ በሁሉም የጤና ተግባራት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።
በተግባሩም ከካፋ ዞን የገዋታ ወረዳ፣ ከቤንቺ ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ እና ከዳውሮ ዞን ማረቃ ወረዳ በክልሉ በጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ አተገባበር ለሞዴልነት የተመረጡ ወረዳዎች እንደሆኑም ኃላፊው ገልፀዋል።
ወረዳዎቹ በመመረጣቸው ለአከባቢው ህብረተሰብ ትልቅ ጠቀሜታ መኖሩን ተረድተዉ የመጣውን እድል በአግባቡ ለመጠቀም ተሳትፏቸውን በእጅጉ ማሳደግ እንደሚገባቸውም አቶ ሀይሌ አሳስበዋል።
በክልሉ ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴንሽን ዘርፍ ኤክስፐርት አቶ ተክሊት ተስፎ በበኩላቸው የማህበረሰብ ተሳትፎ ስልቶችን ማቀናጀት፣ የማስተባበሪያ መንገዶችን መዘርጋትና ማበረታታት የስልጠናው አላማ እንደሆነ አስረድተዋል።
ማህበረሰቡ የግልና የአከባቢ ንፅህና በመጠበቅና በመፍጠር ረገድ ያላቸውን ሚና በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም ተብራርቷል።
በመድረኩ የተገኙ የማረቃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ሀብታሙ ደምሴ የወረዳው አስተዳዳሪ ጽ/ቤት የባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት ማህበረሰቡ በጤና ዘርፍ ተግባራት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን በተገቢው ይሰራል ብለዋል።
በመድረኩ የወረዳው የሴቶች ልማት ማህበር አባላት፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና ሌሎች የባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡ አባይነሽ ወራቦ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የእናቶችንና ህጻናትን ሞት ለማስቀረት የቅድመ ማህጸን በር ካንሰርንና ከቅድመ ወሊድ እስከ ድህረ ወሊድ ያሉትን ምርመራዎች ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የአርባምንጭ ደምና ህብረህዋስ ባንክ በ2017 በጀት አመት ከ6 ሺህ 378 ዩኒት በላይ ደም መሰብሰብ መቻሉን አስታወቀ
ጤናማና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተሰራ ነው – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት