ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዬን ኪሎ ግራም በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገቢያ ማቅርቡን የሸኮ ወረዳ ግብርናና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ት ቤት አስታወቀ

ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዬን ኪሎ ግራም በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገቢያ ማቅርቡን የሸኮ ወረዳ ግብርናና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ት ቤት አስታወቀ

ሀዋሳ፡ ጥር 28/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዬን ኪሎ ግራም በላይ  ቡናን ለማዕከላዊ ገቢያ ማቅርቡን የወረዳው ግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብርት ስራ ጽፈት ቤት አስታወቀ።

ለቡና ጥራት አጠባበቅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም ተገልጿል።

በቤንች ሸኮ ዞን በሸኮ ወረዳ ከ37 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በቡና የተሸፈነ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከ13 ሺህ 470 ሄክታር የሚሆነው መሬት በአርሶ አደሮች ይዞታ እየለማ ያለ መሆኑም ተገልጿል።

ወረዳው በብዛት ቡና የሚመረትበት አካባቢ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ጥራቱን ለማስጠበቅ እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው የቡናና ሻይ ቅመማ ቅመም ምርት ዝግጅት ጥራት ቁጥጥር ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አልኔ እንየው ተናገረዋል።

ቡናን በብዛትና በጥራት አምርቶ ለአለም ገቢያ ለማቅርብ በሚደረገው ርብርብ 17 ሚሊዬን 500 ሺህ ኪ.ግ ጀንፈል ቡናን በታጠበና ባልታጠበ በመሰበሰብ 11 ሺህ 200 ቶን ለማዕከላዊ ገቢያ ለማቅርብ ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነም አስተባባሪው ገልፀዋል።

እስካሁን ባለው ሂደት በወረዳው ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዬን ኪ.ግ በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገቢያ ማቅረብ መቻሉን አቶ አልኔ ተናገረዋል።

ዘንድሮ የአየር ንብረት ለውጥ በቡና ምርት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠሩንና ከዚህ ቀደም ከ8 ነጥብ 5 ሚሊዬን በላይ በታጠበና ባልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገቢያ የሚቀርብ ሲሆን በገንዘብ ሲተመን ከ200 ቢሊዬን ብር በላይ እንደሚሆን አቶ አልኔ አብራርተዋል።

የቡና ጥራትን ለማስጠበቅ ቀድሞ ግብረሀይል በማቋቋም በህገ ወጥ ሥራ ላይም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስተባባሪው አውስተው እስከ 3ኛው ሩብ ዓመት ድርስ የዕቅዳቸውን 80 በመቶ ለማሳካት እንደሚሰሩም ተናገረዋል።

በወረዳው ካሉት 28 የቡና እንዱስትሪዎች  መካከል ሞገስ ይመር የደረቅ ቡና ማበጠሪያ አንዱ ሲሆን ድረጅቱ ከአረም ጀምሮ እስከለቀማ ድረስ በጥራት እንደሚሰራና ከ5ሺህ ኬሻ ቡና በላይ ለማዕከላዊ ገቢያ  እንደሚያቀርቡም የማበጠሪያው ስራ አስኪያጅ አቶ አስማረ ፈጠነ ተናገረዋል።

ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን