ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕፅ ውጠው የተገኙ የብራዚልና የኢንዶኔዥያ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ሀዋሳ፡ ጥር 28/2016 ዓ.2016 (ደሬቴድ) ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕፅ ውጠው የተገኙ የብራዚልና የኢንዶኔዥያ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ ከብራዚልና ከኢንዶኔዥያ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ፖሊስ ከሲቪል አቪዬሽን ደህንነት ዋና መምሪያ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሴኩሪቲ፣ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር በኤክስሬይ ማሽን በተደረገው ፍተሻ ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕፅ ውጠው ስለተገኙ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።
በአጠቃላይ የብራዚል ዜግነት ካላት ተጠርጣሪ በእንክብል መልክ የተዘጋጀ 2.900 ኪሎ ግራም ኮኬይን የተያዘ ሲሆን እስከአሁን ሰባት ፍሬ ኮኬይን ደግሞ ከሆዷ መውጣቱን የገለፀው ፖሊስ ሌላው የኢንዶኔዥያ ዜግነት ያለው ተጠርጣሪ ደግሞ ከዋጠው በተጨማሪ 6.70 ኪሎ ግራም በሻንጣ ውስጥ ሰፍቶ ፍተሻውን ለማለፍ ሲሞክር ከነ-ኤግዚቪቱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው አረጋግጧል።
ምንጭ ፡ ፌዴራል ፖሊስ
More Stories
ከተረጅነት ለመላቀቅ እና በምግብ ራስን ለመቻል ግብርና ዋነኛ መሠረት ነው – የኮሬ ዞን አስተዳደር
ከ360 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ የላብራቶሪ ዕቃዎች ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጋቸው ተገለጸ
ከተለያዩ ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በቡርጂ ዞን በክላስተር እየለማ ያለውን ጤፍ ጎበኙ