በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አቀፍ የሠላምና የሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ጥር 27/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጌዴኦ ዞን ዲላ ማዕከል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አቀፍ የሠላምና የሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተዘጋጀ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አቀፍ የሠላምና የሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የንቅናቄ መድረክ በጌዴኦ ዞን ዲላ ማዕከል መካሔድ ጀምሯል።
“የኢትዮጵያን ሠላም አስጠብቃለሁ ለልጆቼ ምንዳን አወርሳለሁ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ፥ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ሥራ አስፈፃሚ አካላት፣ የክልልና የዞን የሴቶች ሊግ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የወረዳዎች እና ከተማ አስተዳሮች የዘርፉ አመራርና እና አባላት ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ: አማኑኤል ትዕግስቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ከተረጅነት ለመላቀቅ እና በምግብ ራስን ለመቻል ግብርና ዋነኛ መሠረት ነው – የኮሬ ዞን አስተዳደር
ከ360 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ የላብራቶሪ ዕቃዎች ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጋቸው ተገለጸ
ከተለያዩ ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በቡርጂ ዞን በክላስተር እየለማ ያለውን ጤፍ ጎበኙ