የ2016 ተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ መረሃ ግብር በወላይታ ዞን ካዋ ኮይሻ ወረዳ በይፋ ተጀመረ
ሀዋሳ፡ ጥር 27/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በወላይታ ዞን የ2016 ተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ መረሃ ግብር በዛሬው ዕለት በዞኑ ካዋ ኮይሻ ወረዳ በይፋ መጀመሩ ተጠቁሟል።
በዘንድሮ ተፋሰስ ልማት ከ76 ሽህ ሄክታር መሬት በላይ ለማልማት መታቀዱ ተገልጿል።
በመርሃ ግብሩ ከክልልና ከዞን የተወጣጡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የአከባቢው ህብረተሰብ፣ የሐይማኖት አባቶቻችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
እንደ ወላይታ ዞን ከዚህ ቀደም በተሰራው የተፋሰስ ሥራ በአከባቢው የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም የሚያስችሉ ውጤቶችን ማምጣት መቻሉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ተናግረዋል።
በቀጣይም ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ትኩረት በመስጠት ለውጤታማነቱ ተግተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱም 76 ሽህ 9 መቶ 73 ሄክታር መሬት ለማልማት መታቀዱ የተጠቆመ ሲሆን፥ ይህም ለተከታታይ 30 ቀናት በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚከናወን መሆኑ ተመላክቷል።
ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ
መስራት እየቻሉ የገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግሮች ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ቀላል አለመሆኑ ተገለጸ
በስልጤ ልማት ማህበር ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰበሰቡ የአካባቢው ተወላጆች በዞኑ በሚገኙ የላንፉሮ ወረዳና ጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኞችን ተክለዋል ።