በዘንድሮ በጀት አመት በ92 ንዑስ ተፋሰስ 20ሺህ ሄክታር መሬት በተፋሰስ  ልማት ለመሸፈን እየተሠራ መሆኑን የኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ

በዘንድሮ በጀት አመት በ92 ንዑስ ተፋሰስ 20ሺህ ሄክታር መሬት በተፋሰስ  ልማት ለመሸፈን እየተሠራ መሆኑን የኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ

ሀዋሳ፡ ጥር 24/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዘንድሮ በጀት አመት በ92 ንዑስ ተፋሰስ 20ሺህ ሄክታር መሬት በተፋሰስ  ልማት ለመሸፈን እየተሠራ መሆኑን የኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል፡፡

“የተፈጥሮ  ሀብታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል የ2016 ዓ.ም ዞናዊ የአፈርና  ውሃ ጥበቃ ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር  በባካዳውላ ኣሪ ወረዳ ተካሂዷል፡፡

በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ የተሳተፋ አካላት ከዚህ ከዚህ ቀደም የተሠሩ የተፋሰስ  ሥራዎችን ጥበቃ ባለማድረጋቸው የተነሣ መጎዳታቸውን ገልፀው ተፈጥሮን የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፍነታቸውን ለመወጣት  መዘጋጀታቸውን  አስረድተዋል፡፡

የባካዳውላ ኣሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም ባሊ እና የግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገረመው ጋልሻ በጋራ እንደገለፁት፤ የተፈጥሮ ሀብታችን ለብልፅግናችን በሚል መሪ ቃል የዘንድሮውን  ተፋሰስ  ልማት ሥራን በማጠናከር  የተደራጀ ጥበቃም እንዲደረግ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ  ኃላፊ አቶ ታፈሰ ተስፋዬ  በበኩላቸው የተሻለ  አከባቢን ለመፍጠር   ዳገታማና ተራራማ አከባቢዎች ላይ የስነ-አካላዊና ስነ-ሕይወታዊ ሥራዎችን በመጠናከር 20ሺህ ሄክታር መሬት በዘንድሮ የተፋሰስ ልማት ሥራ ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ተግባር  መገባቱን አስረድተዋል፡፡

የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ  አቶ አብርሃም  አታ እንዳስረዱት፤ የተሻለ  ምርት ለማግኘትና  የመሬት መራቆትን ለመከላከል የተፋሰስ ልማት ሥራ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ሁሉም በጋራ አከባቢውን እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን