የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ
የአፍሪካ ሃያላን ብሔራዊ ቡድኖችን በጊዜ ያሰናበተው ሰላሳ አራተኛው የኮትዲቯር አፍሪካ ዋንጫ ሁለት የሩብ ፍጻሜ መርሀግብሮችን ዛሬ ያስተናግዳል።
በዚህም ናይጀሪያ ከ አንጎላ እንዲሁም ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ከ ጊኒ የሚያደርጉት ጨዋታ በሩብ ፍጻሜው ዛሬ የሚጠበቁ መርሀግብሮች ናቸው።
ናይጄሪያ ከ አንጎላ የሚያከናውኑት ጨዋታ፣ ምሽት 2:00 አርባ አምስት ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ባለው በስቴድ ፌልክስ ሀውፎኤት ቦይጅኒ ስታዲየም የሚጀመር ይሆናል።
ምሽት 5:00 በስቴድ ኦሎምፒክ አላሳኔ ኦታራ ስታዲየም ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ከ ጊኒ የሚገናኙበት የእለቱ ሁለተኛው መርሀግብር ነው።
ዘጋቢ: ዘላለም ዳዊት

More Stories
ቼልሲ ማርኮ ፓሌስትራን ለማስፈረም ተስማማ
አበቃለት ሲሉ የሚጀምር፤ ደክሟል ሲሉ የሚበረታው ክርስቲያኖ ሮናልዶ
አርባምንጭ ከተማ ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱ ተረጋገጠ