ዛሬ ምሽት የአፍሪካ ዋንጫ ተጠባቂ ፊልሚያዎችን ያስተናግዳል

ዛሬ ምሽት የአፍሪካ ዋንጫ ተጠባቂ ፊልሚያዎችን ያስተናግዳል

ሀዋሳ፡ ጥር 08/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ)የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ሁሉም ቡድኖች አንድ አንድ ጨዋታ አድርገዋል። ያልተጠበቁ ውጤቶች ፉክክሩን አጓጊ እያደረጉት ነው።

ዛሬ ምሽት እጅግ ተጠባቂ ጨዋታዎችም ይካሄዳሉ ።

አስተናጋጅ ሀገር ኮትድቯር ከናይጄሪያ የሚያደርጉት  ከፍተኛ ትንቅንቅ  በኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።

ሁለቱም ሀገራት አለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ከዋክብትን መያዛቸው ትኩረት ውስጥ እንዲገቡ አደርጓቸዋል።

በመጀመሪያው ጨዋታቸው  ኮትድቯር  ጊኒ ቢሳኦን  ጊኒን ሁለት  ለዜሮ አሸንፋለች ።

ናይጄሪያ ደግሞ ብዙ ተቸግራ ኢኳቶሪያል ጊኒን አንድ ለዜሮ ማሸነፏ ይታወሳል።

ጨዋታው አምስት ሰዓት ጅማሬውን ያደርጋል ።

ጊኒ ቢሳኦና ኢኳቶሪያል ጊኒም ጨወታ አላቸው ።

ዛሬ ምሽት የሚደረገው የጋና እና የግብፅ ፍልሚያም በጉጉት የሚጠበቅ ፉክክር ነው። ሁለቱ ቡድኖች በአፍሪካ ያላቸው ተቀናቃኝነት ተጠባቂ ያደርገዋል።

ጋና በመጀመሪያው ጨዋታ በኬፕቨርዴ ሁለት ለአንድ መሸነፏ የዛሬን ጨዋታ ማሸነፍ ግዴታዋ ይሆናል።

ግብፅ ደግሞ ከሞዛምቢክ ሁለት አቻ ወጥታለች ። በመሆኑም ጋናም ሆነች ግብፅ ከዛሬው ጨዋታ ሙሉ ሶስት ነጥብ ይፈልጋሉ ።

ጨዋታው አምስት ሰዓት ይጀምራል ።

አዘጋጅ : ጀማል የሱፍ