ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የዘንድሮውን የተፋሰስ ልማት ሥራ በይፋ አስጀመሩ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የዘንድሮውን የተፋሰስ ልማት ሥራ በይፋ አስጀመሩ

ሀዋሳ: ጥር 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የዘንድሮውን የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገእቻ ቀበሌ በይፋ አስጀምረዋል::

በማስጀመሪያ መርሀግብር ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፣ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስና ሌሎችም የክልል፣ የዞኖችና እና የልዩ ወረዳው የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል::

ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ