የጌዴኦ ባህላዊ መልከአ ምድር በዮኔስኮ የዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የዕዉቅና መርሃግብር እየተካሄደ ይገኛል
ሀዋሳ፡ ጥር 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጌዴኦ ባህላዊ መልከአ ምድር በዮኔስኮ የዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የዕዉቅና መርሃግብር በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ በጨልባ ቱቲቲ የባህል ቅርስ እየተካሄደ ይገኛል።
የጌዴኦ ባህላዊ መልከአ ምድር በዮኔስኮ የዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል።
በዓለም ቅርስነት የተመዘገበዉ የጌዴኦ ባህላዊ መልከዓ ምድር ቅርስ በዉስጡ ከስድስት ሺህ በላይ የሚሆኑ ትክል ድንጋይ እና ጥምር ደን እርሻ ይገኙበታል።
በህብረተሰቡ ፍላጎት የተሰራና ባህሉን እሴቱን በማኖሮ እያለማ ጠብቆ ያቆየው ባህላዊ መልከዓ ምድር ቅርስ ነው።
በዕዉቅና አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ላይ የፌደራል፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ዱባለ፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ዝናቡ ወልዴ እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ብዙነሽ ዘውዱ
More Stories
“ትንንሽ የሚመስሉ ስራዎች ለትልልቅ ዕድሎች በር ይከፍታሉ” – ወይዘሮ ህልውና ጌታቸው
የህግ ታራሚዎችን በስነ ምግባር ለማነፅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ገለፀ
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች በክህሎት የበቁ ሥራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት ጥራት ያለውን ስልጠና መስጠታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠቀ