የኮሬ ዞን መሠረተ ልማትና ኢኮኖሚ ዘርፍ ከተጠሪ ተቋማት ማኔጅመንት አባላት ጋር የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማ እና የቀሪ ወራት ተግባራት ዕቅድ ላይ ተወያየ

የኮሬ ዞን መሠረተ ልማትና ኢኮኖሚ ዘርፍ ከተጠሪ ተቋማት ማኔጅመንት አባላት ጋር የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማ እና የቀሪ ወራት ተግባራት ዕቅድ ላይ ተወያየ

ሀዋሳ፡ ጥር 21/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኮሬ ዞን መሠረተ ልማትና ኢኮኖሚ ዘርፍ ከተጠሪ ተቋማት ማኔጅመንት አባላት ጋር የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማ እና የቀሪ ወራት ተግባራት ዕቅድ ላይ ተወያይቷል።

አሁን ላይ በአዲስ መልኩ የተደራጁ ወረዳዎች ጠንካራ ሆነው አገልግሎት መስጠት እስኪችሉና የሰው ኃይል እጥረት እስኪሟሉላቸው ድረስ እያንዳንዱ የዞኑ ተቋማት ዩኒትዎች መደገፍ እንዳለባቸው ተገልጿል።

የኮሬ ዞን የፕላን ልማት ዩኒት አስተባባሪ አቶ አስማማው አየለ፤ የ12 ተቋማት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው በተቀመጠው የትኩረት አቅጣጫ መነሻ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በውይይቱ ወቅት በርካታ ተግባራት በተቋማቱ የተፈጸሙ ሲሆን፣ በግብርና ዘርፍ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ውስንነት፣ ለመስኖ፣ ለተፈጥሮ ሀብቶችና ለሌሎችም ትኩረት ያለመስጠት እንደ ክፍተት ተነስቷል።

ከመንገድ መሠረተ ልማት፣ ከገቢ አሰባሰብ ውስንነት፣ ከንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ከኑሮ ውድነት፣ ለባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የትኩረት አለመሰጠትም ስለመኖሩ በሰፊው ተዳሶበታል።

ለዚህም በቀጣይ ወራት ዕቅዶችን በመከለስና ሁሉም የሥራ ባህሉን ቀይሮ በትኩረት መሥራት እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

የኮሬ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ የግብርና መምሪያ ኃላፊ እና የመሠረተ ልማትና የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አስታረቀኝ አንደባ እንዳሉት፤ በጥንካሬ የሚታዩትን ማስቀጠልና በተግባር አፈጻጸም ወቅት የታዩ ክፍተቶችን በባለቤትነት ማረም ያስፈልጋል።

አቶ አስታረቀኝ እንደገለጹት፣ አሁን ላይ በአዲስ መልኩ የተደራጁ ወረዳዎች ጠንካራ ሆነው አገልግሎት መስጠት እስኪችሉና የሰው ኃይል እጥረት እስኪሟሉላቸው ድረስ የእያንዳንዱ ተቋማት ዩኒትዎች መደገፍ አለባቸው።

የምንፈልገውን ውጤት እስክናመጣ እስከ ቀበሌዎች ወርደን ማገዝ አለብን ያሉት አቶ አስታረቀኝ፣ ተክተን ተግባሩን መፈጸም አለብን ብለዋል።

ከግብርና ግብዓትና ሌሎች የኮንትሮባንድ እቃዎችን በመቆጣጠሩ በኩል ፍትሕና ፖሊስን ጨምሮ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚያስፈልግና ተቋማት በመመሪያው መነሻ መሥመር ዘርግተው እንዲንቀሳቀሱ አሳስበዋል።

በዞኑ በክልል አማካኝነት ስለሚሠሩ ፕሮጀክቶች ክትትል ጉዳይ ያነሱት አቶ አስታረቀኝ፣ ተከታትለን ለክልሉ ግብረ መልስ በመስጠት እርምጃ እንዲወሰድ መሥራት አለብን ነው ያሉት።

በሰው ሰራሽ ችግር በሰደድ እሳት ደን ከሚያወድሙ አካላት አካባቢውን በመጠበቅ የአርሶ አደሩ ምርታማነትን መጨመር እንዳለበትም ነው የገለጹት።

ዘጋቢ፡ እስራኤል ቅጣው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን