የግብር ከፋዮች የውይይት መድረክ በዱራሜ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል
ሀዋሳ: ጥር 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግብር ከፋዮች የውይይት መድረክ በዱራሜ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል::
ልማትን ማምጣት ግብርን ከመክፈል ጋር በእጅጉ የተቆራኜ መሆኑን በመድረኩ የተገኙት የከምባታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መለሰ አጭሶ ተናግረዋል::
በታክስ ሥርዓቱ መሠረት ግብር መክፈል ካልቻልን ጉዳቱ መልሶ የእኛው ነው ያሉ ሲሆን የማስተማር እና የመምከር ሥራ ብዙ ጊዜ መከናወኑንም ገልፀዋል::
ከዚህ በኋላ ሁሉም ግብር ከፋይ ግብርን በአግባቡ በመክፈል የሚጠበቅበትን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል::
በግብር ሥርዓቱ ላይ እንቅፋት በሚሆኑ አካሄዶች ላይ ህጉን ተከትሎ እርምጃ ይወሰዳልም ብለዋል::
የዱራሜ ከተማ በክልሉ ካሉ የማእከል ከተሞች አንዷ በመሆኗ ይህን የሚመጥን እድገት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል::
የከተማዋን እድገት ለማፋጠን ደግሞ ግብር መክፈል ወሳኝነት ያለው ነው ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው::
ያለ ደረሰኝ ግብይት መፈፀም፣ የንግድ ፈቃድ አለማውጣት እና ደረሰኝ የመጠየቅ ልምድ አለመዳበር በገቢ ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች መሆናቸው ተገልጿል::
በውይይት መድረኩ ግብር ከፋዮች፣ የከተማ አስተዳደር፣ የዞንና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል::
ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ
More Stories
ቡናን በብዛትና በጥራት በማምረት ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
በደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ በ72 ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ከኮይቤ ማቃና የ12 ነጥብ አምስት ኪሎ ሜትር የመንግድ ግንባታ ስራ ተጀመረ
በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ29 ሺህ በላይ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል