የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎችን እየገመገመ ነው
ሀዋሳ፡ ጥር 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጋሞ ዞን በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎችን እየገመገመ ይገኛል።
በግምገማውም ባለፉት ሰድስት ወራት የተከናወኑ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን በዋናነትም የሌማት ትሩፋት፣ የተፋሰስ ስራ፣ የመስኖ ስራዎች እና ሌሎች ፕሮጀክቶች ይገኙበታል።
በሪፖርቱም በዘርፉ ከዞን አቅም በላይ የሆኑ ስራዎች በክልሉ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራም ተጠይቋል።
በግምገማው የክልሉ ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጠንክር ጤንካን ጨምሮ ሌሎች የቋሚ ኮሚቴ አባላትና የጋሞ ዞን ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሪት አለሚቱ ዮሴፍ እንዲሁም የዞን የዘርፍ ኃላፊዎቸ ተሳታፊ እየሆኑ ነው።
ቋሚ ኮሚቴው በግምገማውም በዞኑ በሪፖርት የቀረቡ ስራዎችን የመስክ ምልከታ ያደርጋል።
ዘጋቢ፡ ቃለአብ ፀጋዬ
More Stories
ክልሉ ከተደራጀ ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች በግብዓት አቅርቦት እና ተደራሽነት የተሻለ ተግባር መኖሩ ተገለጸ
8ኛው ሀገር በቀል ዕውቀቶች ለዘላቂ ሠላም በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የምርምር ዐውደ ጥናት በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል
የፌደራል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የባስኬቶ ዞን ተወላጆች አንድነት እና ወንድማማችነት ማጠናከሪያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል