በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ የበልግ፣ የተፋሰስ ልማት እና ቡና ልማት ሥራዎች የፈፃሚ ማዘጋጃ መድረክ ተካሄደ
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ እንደገለፁት ግብርና ለሀገራችን ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ ዘርፉን በማዘመን የኑሮ ወድነትን ለማቃለል ከፍ ያለ ምርት በማምረት ብልፅግናችንን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ብለዋል።
አክለውም ባለፉት ጊዜያት የተሰሩ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ቢሆኑም ከሚጠበቀው አኳያ ቀሪ ሥራዎች መኖራቸውን ገልፀው፤ የአከባቢዎችን እምቅ አቅም በመለየት እንደሀገር የተያዙ የሌማት ትሩፋት ክላስተሮችን ማስፋትና ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
በተጨማሪም የተፋሰስና የበልግ ሥራዎችን በማጠናከር የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት ሁሉም አካላት እንዲረባረቡም አሳስበዋል።
የኣሪ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታፈሰ ተስፋዬ በበኩላቸው ዞናችን ለግብርናው ልማት ምቹ በመሆኑ ዘርፉን ወጤታማ ለማድረግ ፈፃሚውን በንቅናቄ መምራት አስፈላጊ መሆኑን አሰገንዝበዋል።
በመድረኩም ለተግባሩ ማስጀመሪያ የተለያዩ መነሻ ሰነዶች ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የግብርና ግብዓቶች አጠቃቀም ማሻሻልና ማዘመን እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
ጥራት ያለው ኮረሪማ ለገበያ ለማቅረብና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ትኩረት መደረጉን የአሪ ዞን ቡናና ቅመማቅመም ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የቡና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን አርሶ አደሮች ገለጹ