በሜዳው ሲቪያን ያስተናገደው አርሰናል በሊያንድሮ ትሮሳርድ እና ቡካዮ ሳካ ጎሎች ሁለት ለምንም አሸንፎ ወጥቷል።
ወደ ዴንማርክ አቅንቶ ኮፐንሀገንን የገጠመው ማንቸስተር ዩናይትድ የ4ለ3 ሽንፈት አስተናግዷል።
የማንቸስተር ዩናይትድን 3 ግቦች ራስመስ ሆይሉንድ ሁለቱን ሲያስቆጥር ቀሪዋን ጎል ብሩኖ ፋርናንዴዝ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
ማርከስ ራሽፎርድ በ42ኛዉ ደቂቃ በቀጥታ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
ባየርን ሙኒክ ጋላታሳራይን 2ለ1 አሸንፎ ወደ ጥሎ ማለፍ መግባቱን ሲያረጋግጥ ሁለቱንም የማሸነፊያ ግቦች ሃሪ ኬን አስቆጥሯል።
እስፖርቲንግ ብራጋን በሜዳዉ ያስተናገደው ሪያል ማድሪድ 3ለ0 አሸንፎ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።
ብራሂም ዲያዝ፥ ቪኒሺዬስ ጁኒዬር እና ሮድሪጎ ጎኤስ ለእስፔኑ ክለብ የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥረዋል።
ማንቸስተር ሲቲ፥ አርቢ ሌይፕዚች፣ ባየርንሙኒክ፣ ሪያል ማድሪድ፥ ሪያል ሶሴዳድ እና ኢንተርሚላን ሁለት ጨዋታ እየቀራቸዉ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን ያረጋገጡ ክለቦች ሆነዋል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ዳራማሎ ደንዳሾ ስፖርት ክለብ ባስኬት ቡናን በማሸነፍ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ ሆነ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ለፍፃሜ ያለፉ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል
ስፖርት የወንድማማችነት እና የልማት መጠናከር አንዱ ማሳያ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ