በማህበራትና በዩንየን ተደራጅተዉ የሚሠሩ ቡና አልሚ አርሶ አደሮች በጥራት ማምረትና ማቅረብ ላይ ሁሌም ትኩረት ሊሰጡ ይገባል – የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ

በማህበራትና በዩንየን ተደራጅተዉ የሚሠሩ ቡና አልሚ አርሶ አደሮች በጥራት ማምረትና ማቅረብ ላይ ሁሌም ትኩረት ሊሰጡ ይገባል – የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማህበራትና በዩንየን ተደራጅተዉ የሚሠሩ ቡና አልሚ አርሶ አደሮች በጥራት ማምረትና ማቅረብ ላይ ሁሌም ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባቸዉ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ አሳሰቡ።

የቴፒ ቡና ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩንየን 10ኞ ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በቴፒ ከተማ እህትማማቾች ሆቴል እያካሄደ ነዉ።በጉባኤዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እንደገለጹት ከዞኑ ወደ ዉጭ ከሚላኩ ምርቶች ቡና አንዱ ስለሆነ በዘርፉ የተሰማሩ አርሶ አደሮችና ሌሎች ባለድርሻ  አካላት ጥራት ላይ ትኩረት እንዲሰጡ  አሳስበዋል።

በዞኑ ካለው 85 ሺህ ሄክታር በላይ የቡና ሽፋን ዉስጥ ከ70 ሺህ ሄክታር በላዩ በአርሶ አደሮች ማሣ እየለማ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በጥራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ለድርድር ሊቀርብ እንደማይገባም አክለዋል።

የቴፒ ቡና ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩንየን ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፍቃዱ ደመቀ በበኩላቸዉ ዩንየኑ በ2014 በጀት ዓመት 7.9 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ገልጸዋል።

ዩኒየኑ በሥሩ 29 መሠረታዊ ማህበራትን አቅፎ እየሰራ አንደሚገኝም ተመላክቷል።

በጉባኤዉ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞን ጨምሮ የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ዓለሙ፣ ከየኪ፣ አንድራቻና ማሻ ወረዳዎች መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማህበራት የተዉጣጡና ሌሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ ጌትነት ገረመዉ – ከማሻ ጣቢያችን