የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ጽዱና ውብ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተጠቆመ
የኮሬ ዞን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኞች በወር አንድ ቀን የጽዳት ዘመቻ እንደሚያደርጉም ተገልጿል።
በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሮቤል ዓለም እንደገለጹት የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከህክምና ባሻገር ጽዱና ውብ መሆን ለሠራተኞችም ሆነ ለተገልጋዮች የስነልቦና እና የአእምሮ እርካታን ያስገኛል።
በሆስፒታሉ የጥራት ማሻሻያ ክፍል ተጠሪ አቶ ጥላሁን ሹቴ በበኩላቸው ስለ አካባቢ ንፅህና በቃል ከማስተማር በተግባር ለማሳየት የሆስፒታሉ ሠራተኞች በወር አንድ ቀን የጽዳት ዘመቻ እንደሚያደርጉ ነው የተናገሩት።
አክለውም አቶ ጥላሁን የግልና የአከባቢውን ንጽህና መጠበቅ ከተላላፊ በሽታዎች ራስን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው አስረድተዋል።
ሲስቴር አንድፍሬ ዮናስና ሉቃስ ታደሰ የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች ሲሆኑ የግልና የአከባቢ ንጽሕናን በመጠበቅ የጤና ባለሙያዎችና ተቋማት መልካም ምሳሌዎች መሆን አለብን ብለዋል።
ካነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መምህርት ጥሩወርቅ በቀለ በሆስፒታሉ የተጀመረው የአከባቢ ንፅህና ዘመቻ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመጠቆም ተገልጋዮችም ከሚያዩት መማር እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከፍስሃገነት ጣቢያችን
More Stories
በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሣ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች ደም በመለገሳቸው በደም እጦት ምክንያት የሚሞቱ ወገኖችን ህይወት በማትረፋቸው መደሰታቸውን አስታወቁ
በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ዙሪያ የሚደረገው ጥንቃቄ በመቀዛቀዙ አሁንም የቫይረሱ ስርጭት እየተስተዋለ መሆኑን ተገለጸ
የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የጤናው ዘርፍ ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አደረገ