የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለ6 የፖሊስ ኮሚሽነሮች የረዳት ኮምሽነርነት ማዕረግ ሽልማት ሰጠ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለ6 የፖሊስ ኮሚሽነሮች የረዳት ኮምሽነርነት ማዕረግ ሽልማት ሰጠ

ሀዋሳ፡ መስከረም 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ክልሉ ለ6 የፖሊስ ኮሚሽነሮች የረዳት ኮምሽነርነት ሽልማት መስጠቱ ተመልክቷል፡፡

የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ እና የፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር ሰብስቤ ሻዎኖ ለ6 ረዳት ኮምሺነሮች የማዕረግ ሽልማት በታርጫ ጨከተማ  ሰጥተዋል።

በክልሉ ፖሊስ ኮምሽን የ2015 አፈፃፀም እና የ2016 ዕቅድ ግምገማ ባለ ድርሻ አካላትን በማሳተፍ ለ2 ቀናት ሲካሔድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎ በተቋሙ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉና በአፈጻጸማቸው ከፍተኛ ተቀባይነት ላላቸው 6 የፖሊስ ኮሚሽነሮች የረዳት ኮምሽነርነት ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህም መሠረት፡-

1ኛ ረዳት ኮሚሽነር ከበደ ደበበ

2ኛ ረዳት ኮሚሽነር ዶክተር ካሣ

3ኛ ረዳት ኮሚሽነር በዛብህ ገዝሙ

4ኛ ረዳት ኮሚሽነር ገበራ ገብሬ

5ኛ ረዳት ኮሚሽነር ኃይሌ ጪማ እና

6ኛ ረዳት ኮሚሽነር ኃብታሙ መላኩ ናቸው፡፡

ለበርካታ ዓመታት በፖሊስ ተቋም መስራታቸውንና በሠሩባቸው ዓመታትም ውጤታማ ተግባር መፈጸማቸው የማዕረግ ሽልማት በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።

ለሠራው አካል እውቅና መስጠት ለቀጣዩ ተግባር ይበልጥ የሚያነሳሳ ነው በማለት ለማዕረጉ ያልደረሱ አባላትንም ለውጤታማ ተግባር የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።

ማዕረጉ በክልሉ በአደባባይ ሲሰጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ይህም የፖሊስ ግርማ ሞገስን ከፍ የሚያደርግ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ተገልጿል።

ዘጋቢ፡ ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ጣቢያችን