አረጋዊያዊያንን ለመደገፍ በሚደረጉ ጥረቶቾ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ
ሀዋሳ፡ ጥር 19/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) አረጋዊያዊያንን በሚያስፈልጋቸው ለመደገፍ በሚደረጉ ጥረቶቾ ሁሉም ሰብአዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲስቴር ዘቢዳር ዘውዴ ገለፁ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ “አረጋዊያንን አከብራለሁ፤ በምርቃታቸውም እባረካለሁ” በሚል መሪ ቃል ከኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ መተሰቢያ አደባባይ እስከ አረጋዊያን ማዕከል ግንባታ ስፍራ ድረስ የእግር ጉዞ ተካሄዷል።
የእግር ጉዞ ፕሮግራሙ ዓላማ በሆሳዕና ከተማ እየተገነባ ለሚገኘው የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል ገቢ ማሰባሰቢያ መሆኑ ተመላክቷል።
አረጋዊያዊያንን በሚያስፈልጋቸው ለመደገፍ በሚደረጉ ጥረቶቾ ሁሉም ሰብአዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲስቴር ዘቢዳር ዘውዴ በሆሳዕና ከተማ የአረጋዊያን ማዕከል ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ የእግር ጉዞ መርኃ ግብር ወቅት ገልፀዋል።
ሲስተር ዘቢዳር በመግለጫቸው “ሁላችንም ነገያችንን በማሰብ ለአረጋዊያን መልካም ተግባራትን በመፈፀም በምርቃታቸውም ለመባረክ ሰብዓዊ ግዴታችንን መወጣት ይጠበቅብናል” ብለዋል።
በፕሮግራሙ ላይ አትሌት ጌጤ ዋሚን ጨምሮ ታላላቅ የሀገራችን አርቲስቶችና እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ ዲንና የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ አጠቃላይ ጉባኤ ሰብሳቢ ረዳት ፕሮፌሰር ደበበ ኤሮ የተገኙ ሲሆን በነገው ዕለት በሚካሄደው መርኃግብር ሁሉም በባለቤትነት በመሳተፍ የሰብአዊነት ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የአረጋዊያን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ የተጀመረውን የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል ከፊፃሜ በማድረስ ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንዲቻል በጋራ ልንረባረብ ይገባል ሲሉም አክለዋል።
በመርኃግብሩ ላይ የሀዲያ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ልዑካንን ጨምሮ የተለያዩ የከተማው የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡ አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
በተቋማትና በባለሙያዎች መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን በ2017 ዓ.ም በመኸር እርሻ ከ24 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን አቅዶ እየሠራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ
”የምንተክላቸው ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ ናቸው” – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ