ብራዚል ወደ 2026 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በማጣሪያው መርሃግብር ቦሊቪያን 5ለ1 ስትረታ ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረው በስሙ ያስመዘገበው ነይማር፣ ላለፉት 52 ዓመታት በኤድሰን አሬንቴስ ዶ ናሲሜንቶ ወይም ፔሌ ተይዞ የነበረዉን ክብረወሰን በእጁ አስገብቷል።
የአል ሂላሉ የፊት መስመር ተጫወች ለብራዚል 125 ጨዋታ አከናዉኖ 79 ጎሎችን በማስቆጠር ነዉ የምንግዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ መሆን የቻለዉ ።
ይህን አዲስ ታሪክ ካስመዘገበ በኋላ በሰጠዉ አስተያየት “ሁል ጊዜ የራሴን ታሪክ መስራት እፈልግ ነበር፣ አሁን አድርጌዋለሁ” ሲል ተናግሯል።
ኔይማር ለመራዚል ብሄራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተው እኤአ በ2010 ከአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ጋር በነበረ የአቋም መለኪያ ጨዋታ እንደነበር ይታወቃል።
አዘጋጅ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
አትሌት መሠረት ደፋር የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ሽልማት ተበረከተላት
ማርቲን ኦዴጋርድ ለአንድ ወር ያህል ከሜዳ ይርቃል
ሞሮኮ አሜሪካን በማሸነፍ ለግማሽ ፍፃሜ ደረሰች