የ 2023/24 ዉድድር ዓመት የአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ምሽት መካሄድ ይጀምራል
በ 8 ምድብ የተደለደሉ 32 ክለቦች የአንደኛ ዙር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ እና ነገ ምሽት ያካሂዳሉ ።
በዛሬው እለት ከምድብ 5-8 የተደለደሉ ክለቦች የመክፈቻ መርሐ ግብራቸውን ያከናዉናሉ ።
በምድብ አምስት ፦ 4:00 ፌይኖርድ ከ ሴልቲክ
4:00 ላዚዮ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ
በምድብ ስድስት ፦ 1:45 ኤሲ ሚላን ከ ኒዉካስትል
4:00 ፒኤስጂ ከ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ
በምድብ ሰባት ፦ 1:45 ያንግ ቦይስ ከ አርቢ ሌይፕዚች
4:00 ማንቸስተር ሲቲ ከ ሬድ እስታር ቤልግሬድ
በምድብ ስምንት ፦ 4:00 ባርሴሎና ከ ሮያል አንትዌርፕ
4:00 ሻክታር ዶኔስክ ከ ፖርቶ ይጫወታሉ ።
ለመጨረሻ ጊዜ በ 32 ቡድኖች በሚካሄደው በዘንድሮው የአዉሮፓ ሻምፒዎንስ ሊግ ዉድድር ፣ የጀርመኑ እግርኳስ ክለብ ኡኒየን በርሊን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ፣ የእንግሊዙ ክለብ ኒዉካስትል ከ 20 ዓመታት በኋላ እንዲሁም አርሰናል ከ 6 ዓመታት በኋላ ይሳተፋሉ ።
የዚህ ዓመት የፍፃሜ ዉድድር በዌምብሌይ እንደሚካሄድ ያሳወቀው የአዉሮፓ እግርኳስ ማህበር ከሚቀጥለው የዉድድር ዓመት ጀምሮ የተሳታፊ ክለቦች ቁጥርም ወደ 36 ከፍ እንደሚል ማሳወቁ አይዘነጋም ።
አዘጋጅ ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች