ኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት ተጨማሪ ሜዳሊያ ትጠብቃልች !!!

ኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት ተጨማሪ ሜዳሊያ ትጠብቃልች !!!

19ኛዉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዎና መካሄዱን ቀጥሏል ።

በሃንጋሪ ቡዳፔስት ከተማ በመናወን ላይ የሚገኘው ሻምፒዮናው ዛሬ በአረተኛ ቀን ዉሎዉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው ሁለት የፍፃሜ ዉድድሮች ይካሄዳሉ ።

የሴቶች 1500 ሜትር እና የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ፍፃሜ ከወዲሁ ወድድሮች የበርካቶችን ትኩረት ስበዋል ።

ምሽት 4:30 ሲል በሚጀመረው በሴቶች 1500ሜትር የፍፃሜ ዉድድር ላይ ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ሃየሎም ኢትዮጵያን በመወከል ይወዳደራሉ ።

እንደ አዉሮፓዊያን አቆጣጠር በ 1997 አቴንስ በተደረገዉ ወድድር በርቀቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳፈችዉ ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በኋላ በሲቪያ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዎና የመጀመሪያውን ሜዳሊያ (ነሃስ ) በአትሌት ቁጥሬ ዱሌቻ አማካኝነት አገኘች ።

በ2015 እኤአ በጂንግ ላይ በገንዘቤ ዲባባ የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ በ 1500 ተገኝቷል ። አስካሁን አራት ሜዳሊያዎች በርቀቱ ኢትዮጲያ አግኝታለች ። ገንዘቤ ዲባባ (2015) ወርቅ ፣ ጉዳፍ ፀጋዬ (2022 ኦሪገን) ብር እና (2019ዶሃ ) ነሃስ እንዲሁም ቁጥሬ ዱሌቻ (1999 ሲቪያ ) የነሃስ ሜዳሊያን ለሃገራቸዉ ማምጣት ችለዋል ።

ዛሬ ምሽት በሚደረገዉ የፍፃሜ ዉድድር ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተጨማሪ የርቀቱ የክብረወሰኑ ባለቤት የሆነችዉ እንዲሁም የ2017 እ 2022 የሻምፒዮናው አሸናፊ ኬኒያዊቷ አትሌት ፌይዝ ኪፕዬጎን እና የ2019 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዎና የ1500ሜትር አሸናፊዋ ሲፋን ሃሰን በፍፃሜው ዉድድር ተሳታፊዎች ናቸዉ ።

ምሽት 4:42 ሲል በሚካሄደዉ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ዉድድር አትሌት ለሜቻ ግርማ እና አትሌት ጌትነት ዋለ ኢትዮጲያን ወክለዉ ይሮጣሉ ።

በጥሩ አቋም ላይ የሚገኙት አትሌቶቹ ለኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ዉድድር ተሳትፎ ታሪክ በርቀቱ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ለማምጣት እያለሙ ወደ ዉድድሩ ይገባሉ ።

በሶስት ትልልቅ ዉድድሮች ማለትም እኤአ 2019 በዶሀ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዎና ፣ በ 2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ እና በኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሃገሩ የብር ሜዳሊያ ማምጣት የቻለው እና የወቅቱ የርቀቱ የክብረወሰን ባለቤት ለሜቻ ግርማ ከሞሮኮዋዊው ሶፊያን ኤልባካሊ ጋር የሚያደርገው ትንቅንቅ ከወዲሁ አጓጊ ሆኗል ።

በዶሃ ፣ ቶኪዮ ኦሊምፒክ እና በኦሪገን ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዎና አራተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለሃገሩ ዲፕሎማዎችን ያስገኘዉና 8:05.15 የዓመቱ ምርጥ ሰዓት ያለዉ ጌትነት ዋለ የተሻለ ደረጃ ይዞ ሊያጠናቅቅ እንደሚችል ተገምቷል ።

የኬኒያዊያን የባህል እስፖርት ነዉ ተብሎ የሚነገርለት የ3000 ሜትር መሰናክል በቅርብ ዓመታት ዉስጥ ግን ከእጃቸዉ እየወጣ ይገኛል ። ከ18 የዓለም አትሌቲክ ሻምፒዎና በርቀቱ 13 ያሸነፉት ኬኒያዊያን ናቸው ። ዘንድሮስ ምን ያስመዘግቡ ይሆን ? ሲሞን ኪፕሮፕ ኮእች ፣ ቤንጃሚን ኪጋን እና አብርሃም ኪቢዎት የኬኒያን ክብር ለማስመለስ እያሰቡ ይወዳደራሉ ።

አዘጋጅ ፡ ሙሉቀን ባሳ